ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
60

በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት ለተሁለደሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ የተቋራጭ ደረጃውን የሚያሟሉ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የግንባታ ተቋራጭ ደረጃቸዉ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  4. የመልካም ስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውንና ተፈላጊ መረጃዎችን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦ ወይም (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተቋራጭ በሚሞላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ያልተሟላ ያቀርቡ እንደሆን ጨረታው ተቀባይነት የለዉም፡፡
  9. ተቋራጮች የዋጋ ማቅረቢያ በታሽገ ኢንቨሎፕ የማወዳደሪያ ዋጋቸዉ ኦርጅናል እና ኮፒ ማለት ማስታወቂያው ከወጣበት ከጥር 11/2018 እስከ የካቲት 09/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 መ/ቤቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  10. ጨረታዉ የካቲት 9/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ይክፈታል፡፡
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓትን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
  12. ተቋራጮች የቢሮ ግንባታ ስራ አገልግሎት ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ዉስጥ አንድ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋን እንድሁም ቀን ፈርማና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል፡፡
  13. የቋራጮች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትት ወይም የማያካትት መሆኑን መግለጽ አለባቸዉ፡፡
  14. በጨረታ ሂደቱ ላይ የ2014 የግንባታ መመሪያ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  15. አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ድምር ዋጋ ነው፡፡
  16. በሰነዱ የተዘረዘሩትን የግንባታ ሥራዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀው መሰረት የመስራት ግዴታ አለበት፡፡
  18. ተቋራጮች የሞሉት ዋጋ ከመሃንድስ ግምት በላይ ከሆነ በመመሪያው መሰረት ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችለም፡፡
  21. ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here