ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

የቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለቋሪት ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቋሪት ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት 3፡30 ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ይታሸግና ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ጽ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
  11. በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ፓራፍ ማድረግ አለበት፡፡
  12. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎች እና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  13. አሽናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል መያዝ አለበት፡፡
  14. የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ካቀረበው ድርጅት ሲሆን ከአንድ ሎት ከፋፍሎ መሙላት ወይም መጫረት ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  15. አሸናፊው ያሽነፈውን ዕቃ ቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 46 02 26 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here