ጨረታ ቁጥር ባምማ/ሽ08/2018
በኢትዮጵያ ግብርና ስታዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ቅርንጫፍ /ጽ/ቤት በሰሜን አቸፈር ወረዳ በቁንዝላ ከተማ በሚገኘው በድሮው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር እርሻ ልማት ግቢ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ የትራክተር፣ ኮምባይነርና የተቀጽላ መሳሪያዎች ብረታ ብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከታች የተቀመጡት የመወዳደሪያ መስፈርቶችን በጥንቃቄ በማየት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
- የተጠቀሰው የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች የሚገትው ቁንዝላ ከተማ ምርጥ ዘር ግቢ ውስጥ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ ባገለገለ እቃ፣ ውድቅዳቂ ወይም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የምትገዙበትን ዋጋ በኪሎ ግራም ሂሳብ ባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው ቅጽ ወይም ፎርም መሰረት ቫት ጋር ሞልታችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ንብረቱ በሚገኝበት ቁንዝላ ከተማ የድሮው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ግቢ በመሄድ በአካል በማየት በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የአንድ ኪሎ ብረታ ብረቶችን የምትገዙበትን የዋጋ መጠን ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ከጥር 11/2018 እስከ ጥር 21/2018 ዓ.ም ድረስ የሚውል ሲሆን ጨረታ የሚዘጋው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 በቅ/ጽ/ቤቱ ሆኖ የሚከፈተውም በዚሁ ቀን በ8፡30 በባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚውል ሆኖ መጫረት የምትፈልጉ በሙሉ በመንግስት ሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ክፍት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስያዝ አለበት፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 16 ጉደር ዱቄት ፋብሪካ በስተጀርባ ሲሆን የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 78 74 49 59 ወይም 09 82 21 21 20 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን

