የአብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የጽህፈት እቃዎች ፣ እና ሎት 4 የመኪና ዲኮር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል በአብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 307 ዋና ገንዘብ ያዥ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት አይነት ጨረታ የሞሉትን ጥቅል ዋጋ አንድ በመቶ በባክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒ.ኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዘው ገንዘብ በአብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻው በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አሰተዳደር ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 307 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በስራ ሰዓት ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ድረስ ማሰገባት ይቻላል ወይም ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ኮፒ ማሰገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 309 የጨረታ ጋዜጣው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛው እቃ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ጥራት ያለው እቃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ መ/ቤቱ ከሚፈልግበት ቦታ አብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት ድረስ ሊያቀርብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሎት የተዘረዘሩትን ሁሉንም እቃዎች መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ የውድድር ሥርዓቱ ግን በሎት ወይም በድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ሁሉንም አይነት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- በሚቀርበው እስፔስፊኬሽን መሰረት የምታቀርቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ቢሮ ቁጥር 307 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 37 91 በመደወል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የመ/ቤታችን አድራሻ ቀበሌ 16 ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙሰና ኮሚሽን ህንጻ 3ኛ ፎቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአብክመ ሚሊሻ ጽ/ቤት

