የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዋድላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የውሃ ዕቃ፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 የመኪና እቃ ሎት 6 የመኪና ጎማና ባትሪ፣ ሎት 7 የጫማ ደንብ ልብስ፣ ሎት 8 የተዘጋጁ የደንብ ልብስ፣ ሎት 9 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 10 ፈርኒቸር፣ ሎት 11 ሲሚንቶ እና ሎት 12 የስፖርት ዕቃና ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች /ድርጅቶች/ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በአዲሱ የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ይህ ግልጽ ጨረታ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትንና ዋጋ የሞሉበትን ሙሉ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ናሙና መያዝ ለሚያፈልጋቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማየት ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በመመሪያው መሰረት ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 /09 12 89 76 71 /09 35 21 60 96 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት