ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
64

ቁጥር አካ/ጥ/ግ/3/2018

የአብክመ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና ሀብት ስራ ማህበራት ኮሚሽን በመደበኛ በጀት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ ፈርኒቸርና የመኪና ዲኮር እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ  ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የጨረታውን ሠነድ ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15  ተከታታይ  ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጋንቢ ጎን ካለው የአካ/ጥ/ባለስልጣን መ/ቤት አዲሱ ህንፃ ግራውንድ ላይ  ግዥ ቢሮ በመምጣት 100 ብር በመክፈል  መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታው ሠነድ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን እስከሚዘጋበት 3፡00 ድረስ ግዥ ቢሮ አጠገብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. በጨረታ መዝጊያው ቀን 3፡01 ታሽጐ 3፡30 ተጫራቶችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን በመ/ቤቱ ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ከ20 ሽህ ብር በላይ ለሆኑ ግዥዎች ቫቱን በግማሽ በመቶና ለአገልግሎት ግዥ 10ሺ ባላይ ለእቃ ግዥ ከ20ሺ በላይ ለሆኑ ግዥዎች ሶስት በመቶ ዊዝሆልዲንግ ታክስ ቢሮው ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  8. መ/ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት በነጠላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 62 06/09 11 59 75 82 ይደውሉ፡፡

 

የአብክመ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here