ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
77

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ፋ/ን አስ/ቡድን ለመስሪያ ቤታችን አገልግሎት የሚውሉ 1. ብትን ጨርቅ፣ 2. የውሃ እቃዎች፣ 3. የአገር ውስጥ እና የውጭ ፈርኒቸር፣ 4. ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች 5 የመኪና እቃዎች፣ 6. የህንፃ መሣሪያዎች፣ 7.የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ 8. የቢሮ መጋረጃዎች፣ 9. የድምጽና ምስል እቃዎች፣ 10. የተዘጋጁ ልብሶች እንዲሁም 11. የታሸገ ውሀ ለመግዛት በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የሚገዙት እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ የያዘ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ሰነድ ከምሥራቅ ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት ብር 50 (አምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃዎች ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ከግዥ ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ከአሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  11. አሸናፊው እቃዎችን ምሥ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ቢሮ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ መቀነስም ሆነ መጨመር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በዚህ ያልተጠቀሱ በግዥ መመሪያው የተቀመጡ የተጫራቾች መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 55 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የምስራቅ ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here