ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

የጨረታ ቁጥር 03/2018

ኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉና ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የሰራተኞች የደንብ ልብስ (ብትን ጨርቆች) የተዘጋጁ ሸሚዞች፣ ሎት 2 ቧንቧና መገጣጠሚያ እንዲሁም ሎት 3 የውሃ ጥራት ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራች ሁሉ ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙበትን የዕቃዎች የጠቀሜታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ናሙና ወይም ብሮሸር ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምኘል ወይም ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካሉን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ፋይናንሻሉን ሲፒኦውን ጨምሮ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ለየብቻ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የጨረታ ሰነዱን 4፡00 ድረስ በማስገባት ከቀኑ 4፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ ኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስልክ ቁጥር 033 551 02 72 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here