ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ ሎት 1 ከቡሬ ከተማ ወደ ወረታ 17,300 ኩ/ል ሰብል፣ ሎት 2 ስኳር እና ዘይት አዲስ አበባና ከተለያዩ ከተሞች ወደ ቡሬ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የደረቅ ጭነት ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉና የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሞላ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች አንድ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብ ወይም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፓስታው ውስጥ ማስገባት እና ፓስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ  በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  8. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  9. አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው  ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. የሰብል ማጓጓዝ ጨረታ አሽናፊው በውሉ በሚሰጠው ጊዜ ማጓጓዝ (ማንሳት/ አለበት፡፡
  11. ስኳር እና ዘይት ለአንድ አመት ማጓጓዝ የሚችል፡፡
  12. ተጫራቹ በራሱ ስም የተዘጋጀ የማጓጓዣ ሰነድ /ዲስፓች/ ማዘጋጀት አለበት፡፡
  13. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ እና የቀረጽ ወጭወችን መሸፈን አለበት፡፡
  16. ለተጫራቾች ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 058 774 640 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here