ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
100

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ሂደቶችና ለምድብ ችሎቱ አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን በመግዛት ማለትም፡- ሎት 1 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 2 ሸሚዝና ጫማ፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የህትመት ዉጤቶች፣ ሎት 5 ነዳጅና ቅባት፣ ሎት 6 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 7 ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 9 የመኪና ጎማ፣ ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 11 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 12 በአገር ዉስጥ የሚሰሩ ወንበሮች፣ ሎት 13 የህንፃ መሳሪያዎች እና ሎት 14 የሶፋ ልብስና መጋረጃ ለመግዛት መስፈርቱን አሟልተዉ ከሚገኙ አቅራቢዎች /ድርጅቶች/ መካከል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ሥለዚህም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ያሳደሱ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘዉ የምያቀርቡ ሲሆን ግዥዉ 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ለሚፈፀሙ ግዥዎች እና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለአያንዳንዱ ሎት የማይመስስ00 /ሰላሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከማ/ጎን/ ከፍ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታዉ ከህዳር 9/2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በአየር ላይ ቆይቶ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ከቀኑ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ማ/ጎ/ዞን/ከ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታን ከመክፈት አያግድም፡፡
  3. የዕቃ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ሙሉዉን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር የደረሠኝ ኮፒ በማሸግ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  5. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ዋና ሠነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ ቦታ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዣና እንዲሁም ማናቸዉም የመንግስት ታክስን ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
  7. መሥሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ዉድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  8. ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካለዎት ግዥና ፍይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 44 40 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here