የጨረታ ቁጥር 23/2018 ዓ.ም
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የተለያዩ የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለማቅረብ የሚሳተፋ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነድ በተለያዩ ፖስታ ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቸች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50.ዐዐ/ሃምሳ ብር/ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ)፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለማቅረብ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ)፤ ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለት ከጥር 18/5/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 2/2018ዓ/ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን የካቲት3/2018 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ

