የቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በተያዘዉ በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. የፅዳት ዕቃዎች፣ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት4. የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልታችሁ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200‚000 (ከሁለት መቶ ሽህ ) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ዋናዉንና ኮፒዉን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ (ሰነድ) ስማቸዉን፣ ፊርማቸዉን እና ሙሉ አድራሻቸዉን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ያረፈበትና የጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀበት ቋንቋ በመጠቀም ሞልተዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በወቅቱ በመምጣት ለሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታውን ሞልተዉ በሆስፒታላችን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 94 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታዉ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡20 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በሰዓቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም መ/ቤቱ ሂደቱን ጠብቆ ጨረታዉን የሚከፍት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ወቅት ለማጭበርበር ወይም የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ከሆነ ከጨረታዉ ዉጭ እንደሚሆኑ፣ ለወደፊትም በተቋማችን የግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ የማገጃ ደብዳቤ እንደሚፃፍባቸዉ እና ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱት በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ በግዥ ሂደቱ ላይ 20በመቶ ከፍና ዝቅ ብሎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በ 09 10 34 04 95/09 14 46 07 00 ይደዉሉ፡፡
የቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

