ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
38

በሰሜን ጎጃም ዞን የአዴት ከተማ አስተዳደር የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ሎት1.ብትን የደንብ ልብስ ጣቃ፣ ሎት2.የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ  እቃዎች ላፕቶፕ ኮምፒውተር ጨምሮ፣ ሎት4. የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት5. የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት6. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት7. የግብርና ዕቃዎች፣ ሎት8. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት9 ኬሚካል፣ ሎት 10. የመኪና ጎማ እና ሎት11.የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡   

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ  ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ  ዋስትና  ለሚወዳደሩበት ዕቃ  የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። በ16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ስም አድራሻ የሚመለከተው  ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጦ ማቅረብ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች በዘርፉ እንዲወዳደሩ የሚያስችል ንግድ ፈቃድ ካላቸው ከአንድ በላይ ሎት መወዳደር ይችላሉ።
  13. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል መስከበሪያ 10በመቶ በሲፒኦ በማስያዝ ውል መፈፀም ያለባቸው ሲሆን፤ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ማዕከሉ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ አካል ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከክፍሉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም   በስልክ ቁጥር 058 338 11 66 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  15. ተጫራቾች አሸናፊውን በሎት ለመለየት ያመች ዘንድ በአንድ ሎት ለቀረቡት ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

          የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here