ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል ለማዕከሉ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኮምፒተር ዕቃዎች ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4  የፈርኒቸር ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 5 የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 6,000 (ስድስት ሽህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታውን ሰነድ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ከጥር 25/2018 እስከ የካቲት 09/2018 ዓ.ም ለተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን የካቲት 10/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጨረታው ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ግዥና ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በሌላ ሰው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 74 87 ወይም 09 18 03 23 67 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. አድራሻችን ጎንደር ቀበሌ 18 ከፍሎሪዳ ሆቴል ፊት ለፊት ወደ መስጊድ በሚወስደዉ መንገድ ከአቶ አብይ ምትኩ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማእከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here