የሰሜን ወሎ ዞን ፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ፍይናስ ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች ማለትም ሎት 1 PPC ሲሚንቶ፣ ሎት 2 ጥራቱን የጠበቀ የግንባታ ድንጋይ እና ሎት 3 ጥራቱን የጠበቀ ንጹህ የወንዝ አሸዋ በግልጽ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል::
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው::
- የግዥ አገልግሎት መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዝጋቡ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ የሚችል የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒ በስም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /እስቴስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ሎት በማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ /የእቃውን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለፍ/ገ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ ተቆርጦ ኮፒውን ወይም የጥቃቅን ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልግ የጨረታ የጥቃቅን ተጠቃሚ ከሆኑ ልዩ ድጋፍ ሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱ የአየር ላይ ቆይታ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ከ30/07/2016 ዓ/ም እስከ 14 /08/2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱ ከፍላቂት ገረገራ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይቻላሉ::
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- አንዱ ተጫራች በአንዱ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም::
- እንደ በጀት አቅም ሃያ በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን በሟሟላት ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዌ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ 3፡30 ይከፈታል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ስዓት ተዘግቶ በዚሁ ስዓት ይከፈታል::
- አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበርያ አስር በመቶ ለፍ/ገ/ከ;አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል:: በተባለው ቀን ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል::
- አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የአሸነፋቸውን እቃዎች በፍላቂት ገረገራ ከ/አስ/ ባሉት ቀበሌዎች ድረስ አጓጉዞ ያቀርባል\::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0332110528 እና በ0332110089 በመደወል ማግኝት ይችላሉ::