ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት አመት በካፒታልና በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሰረተ ልማት የግንባታ ሥራዎች፣ የድልድይ እና የጋቢወን፣ የእቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ ለግንባታ ሥራ የተለያየ ደረጃ ባላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሁለት ሳይት የድልድይ ግንባታ ሥራ በመደበኛ በጀት፣ የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ከሎት 1-4 በመደበኛ በጀት፣ ሎት 1. እና 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በመደበኛ በጀት እና ሎት 1. እና 2 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ በመደበኛ በጀት የተለያዩ ደረጃዎች ባላቸው የሥራ ተቋራጮችና አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑትን የግንባታ ማቴሪያሎትና የእጅ ዋጋ ችለው ለሚሰሩ ተወዳዳሪዎችና የእቃ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችና አቅራቢዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ስለዚህ፡-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ/ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ/ ገቢ ሆኖ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለድልድይ ግንባታ ሥራ አይሴማ ጦጢት ወንዝ 450,000.00፣ ለድልድይ GTZ /ጅቲዜድ/ ቤት እስከ ጎማጣ መሻገሪያ፣ 250,000.00 የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ለሎት 1፣ 60,000.00፣ ለሎት 2 ብር 40,000.00፣ ለሎት 3 ብር 65,000.00 እና ሎት 4 ብር 50,000.00፣ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 5,000.00 ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ 3,000.00፣ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ  3,000.00፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ 6,000.00 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር ለድልድይ ግንባታ ሥራ 00 /ሶስት መቶ ብር/ ለጋቢዮን ግንባታዎችና ዕቃ ግዥዎች 150.00 አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝቶ መጫረት /መወዳደር/ የሚችለው የመረጡትን የግንባታ ሥራ ለድልድይ ግንባታ ሥራ 1 ሳይት ብቻ፣ ለጋቢወን ግንባታ ሥራ 2 ሳይት ብቻ መርጦ መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ወይም ከተፈቀደው ሰነድ በላይ ገዝቶ የተገኘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡ ለአዲስ ግንባታ ሥራ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ከሆኑ የማቴሪያል ቴስት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም የግዥ ወይም የግንባታ ስራዎች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ መሙሊያ ላይ ምንም አይነት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ የማይነበብ ተደጋግሞ የተጻፈ እንዲሁም የማይነበብ የማስረጃ ፎቶ  ኮፒ አያይዞ የቀረቡ ተወዳዳሪዎች /ተጫራቾች/ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናልና በኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ሳይት ወይንም እቃ በፖስታው ላይ በመጻፍና በማዘጋጀት የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ በተለያየ ፓሰታ አሽጎ ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት  በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን  ማሰገባት ይኖረባቸዋል፡፡
  10. በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ለተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ወቅታዊ የሆነ መረጃ በሃላፊ የተፈረመ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  12. የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ሥራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡
  13. ጨረታው ተግባራዊ የሚሆነው መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በ2014 ግንቦት ወር ላይ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የግዥ መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ ወይም መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. ተጫራቾች የተሳሳተ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ በህግ ያስቀጣል ከጨረታውም ውድቅ ይደረጋል፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 የተዘረዘሩት መስፈርቶች ለሁሉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪዎች) ገዥ ይሆናሉ፡፡

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here