ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

የባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለመደበኛ ሰልጣኞች ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የህንጻ ግንባታ እና የውሃ ዕቃዎች ሎት2. የልብስ ስፌት እና የጋርመንት እቃዎች ፣ሎት3. አውቶሞቲቭ ጥሬ እቃዎች፣ ሎት4. የተለያዩ ብረቶች፣ ሎት5. የአይ ሲቲ ጥሬ እቃዎች፣ ሎት6 .የግብርና ጥሬ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ  የማይመለስ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ  አለባቸው፡፡
  5. ጨረታውን ሲሞሉ በፖስታው ላይም ሆነ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
  6. ጨረታውን በሚሞሉበት ጊዜ በጨረታ ዋጋው ማቅረቢያ ላይ ምንም አይነት በነጠላም ሆነ በጥቅል ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  7. ጨረታውን በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
  8. እያንዳንዳቸውን እቃ ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ3ወር የሚቆይ (ቢድ ቦንድ) ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒዩ) በማስያዝ በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታው ያሸነፈው ድርጅት ንብረቱን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ በሙያተኛ በማረጋገጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ለተጨማሪ መረጃ በፋክስ ቁጥር 058 218 0578፣በስልክ ቁጥር 058 218 05 74 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የባሕርዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here