ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

በአ.ብ.ክ.መ. ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደ/ማርቆስ ቅርንጫፍ መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚዉሉ በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና የላቦራቶሪ ሪኤጀንት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ሠነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከተቋሙ ቢሮ በመቅረብ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መዉሠድ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነ ቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ተቋሙ በር ላይ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ 3፡35 ላይ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ፖራፍ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ምድብ በድምር ዋጋ ስሌት ይሆናል፡፡
  11. የአሸነፈውን እቃ በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊው ከተለዬ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት እስከ 20 በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
  14. ጨረታው በሎት ስለሆነ የገዙት ሰነድ ላይ የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ተቋሙ የሚሰበስበው 3 በመቶ ዊዝ ሆልድ ብቻ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ የውሃ ማጠራቀሚያው ጋን አጠገብ ደ/ማርቆስ

የአ.ብ.ክ.መ. ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደ/ማርቆስ ቅርንጫፍ መ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here