- የድልድይ ግንባታ ሥራ በመደበኛ በጀት፡-
የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የድልድይ ግንባታ ሥራ አይሴማ ጦጢት ወንዝ በቁጥር 1 ኮድ woldia–CW-B-cip–02—01-2024/2025 ያለውን የድልድይ ግንባታ ሥራ በደረጃ 6 እና በላይ ሙያ ባላቸው GC ፣ GTZ /ጅቲዜድ/ ጎማጣ መሸጋገሪያ ቁጥር 1 ኮድ woldia– CW-B-cip-02-02 – 2024/2025 ያለውን የድልድይ ግንባታ ሥራ በደረጃ 6 እና በላይ ሙያ ባላቸው GC ተቋራጮች፣ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በሚቀርበው የመደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት የተሟላ መረጃ በተለያዬ ፓስታ በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ስለዚህ ለድልድይ ግንባታ ሥራ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የግንባታ ማቴሪያሎችና የእጅ ዋጋ ችሎ ወይም አቅርቦ ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በተዘጋጀው ፕላንና የሥራ ዝርዝር እና ዲዛይን መሰረት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/04/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለብዎት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን አይሴማ ጦጢት ወንዝ ድልድይ 09/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
GTZ /ጅቲዜድ/ ጎማጣ መሸጋገሪያ ድልድይ ደግሞ በዚሁ ቀን 09/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ሎት 1 እና ሎት 2 /በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ/
የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሠራው የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ሎት 1 905 ሜ ኮድ woldia-—GB—cip–05-01-2024/2025፣ ሎት 2 550 ሜ ኮድ woldia-GB—cip-06-01-2024/2025 እና የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10/04/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 10/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- የጋቢዮን ግንባታ ስራ ሎት 3 እና ሎት 4 /በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ/
የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሠራው የጋቢዮን ግንባታ ሥራ ሎት 3 960 ሜ ኮድ woldia—GB—cip–07-01-2024/2025 የጋቢዮን ግንባታ ሥራ፣ ሎት 4 762 ሜ ኮድ woldia—GB-cip–08-01-2024/2025 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 11/04/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 11/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ