በአዊ ብሄረሰብ ዞን የዳንግላ ከተማ መጠጥ ዉሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ሎት 1. ቧንቧ እና መገጣጠሚያ ዕቃዎች ፣ ሎት 2. ኤሌክትሪካል መለዋወጫ እቃዎችን፣ ሎት3. ፓምፕ እና ኤሌክትሮ መካኒካል መለዋዎጫ እቃዎች፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ ( ብትን ጨርቅ፣ ጫማ፣ ተሰፍተው የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችን ወዘተ…) ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺ) ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ውድድሩ በሎት መሆኑን በማወቅ የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ይሆናል ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡00 መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ እስከ 3:30 ተጫራቾች ጨረታውን በማስገባት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የድርጅታቸውን ማህተም ፣ስማቸውን ፣ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ )ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ሁለት በመቶ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ወይም በድርጅታችን ደረሰኝ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በአሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በመቤ/ቱ ደረሰኝ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከተጠየቀው እቃ ውስጥ ድርጅቱ 25በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ወጭ ዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በማምጣት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 18 71 01 53 ወይም 09 18 71 01 56 ደዉለዉ ወይም የገቢ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በአካል በመቅረብ መረዳት ይችላሉ፡፡
የዳንግላ ከ/ መ/ ዉ/ እና ፍ/ አገ/ ድር

