ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
27

በማዕከላዊ ጐንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሎት 1. G+2 ቢሮ ግንባታ መሃንዲስ ባወጣዉ የሥራ ዝርዝር እና ዲዛይን መሰረት የእጅ ዋጋ እና ጥሬቃን ጨምሮ /ጥቅል ዋጋ/ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  5. ሁሉም ተጫራች የመልካም ሥራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና በህንጻ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ሆነዉ በዘመኑ የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸውጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 0.5 ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ከ90 (ዘጠና) ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ሰነዱን የቴክኒካል እና የፋይናሻል ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሸ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናሻል ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ታሽጎ በ31ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  12. የስራዉ ዝርዝር (ሰፔስፊኬሸን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058 448 02 34 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠዳ ጤና ሳ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here