የባህር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት2. የፅዳት ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፤ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን ) ካርድ ወይም ሰርቲፍኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ለዕቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩ የዕቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡ ውድድሩ በሎት ጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሀምሳ) ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስተና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውንም ግብር ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በደም ባንኩ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ሁለት በመቶ በማስያዝ ከዋናው ፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርብዎታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በቀረበው የመጫረቻ ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሰረት ብቻ የአንድ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደም ባንኩ የግዥ ኦፊሰር ቢሮ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደም ባንኩ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ቢሮ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 15 37፣ 058 220 74 03 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ቀበሌ 08 ከሰላም ካምፓስ ፊት ለፊት የድሮው አውስኮድ ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡
የባህር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት

