ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1. ኤሌክትሮኒክስ፣ 2. ፓምፕ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ለእያንዳንዳቸው በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለተ.ቁ 13,000 (አስራ ሶስት ሽህ ብር)፣ ለተ.ቁ 2. 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዛ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ /ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 /አንድ/ በ16ኛው ቀን/ አስራ ስድስተኛው / ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጫረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎችን ወረዳው ለማንኛውም አገልግሎት የሚከፈለውን ወጭ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችልና ለማንኛውም የሚከፈለውን ወጭ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አቤቱታ ወይም ቅሬታ  ካላቸው በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች 20በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  16. የጨረታ መክፈቻ ቀነ በዓላት ፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  18. ከአሸናፊው ድርጅት ሶስት በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  19. ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምገም ፤ለማጽደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጀቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ለ40ቀን ይሆናል፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 664 04 64/002 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡

የጎንቻ /ሲ/እ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here