የአማካሪዎች የፍላጎት መግለጫ/ Request for Expression of Interest Consultancy service/
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በመደበኛ በጀት በ2017 በጀት ዓመት የድዛይንና የEIA ሥራ /short list/ በማድረግ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሥራዉ አላማ፡- ለተጠቀሰዉ ሥራ የland fill, የወጭ መብራት ዝርጋታ፣ ግሪን ኤሪያ፣ የወልድያ ከተማ የሚገልጽ ሎጎ እና ዘመናዊ ቄራ ድዛይንና የማማከር ሥራ በሎት ለሁሉም ሥራዎች የEIA/አካባቢና ማህበራዊ ተጽኖ/ ሥራ መስራት ይሆናል፡፡ ዝርዝር ሥራዎች በቢጋር/TOR/ ላይ በመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ /Request for Proposal/ ሰነድ ዉስጥ ተዘርዝሮ ቅድመ መረጣውን ለሚያልፍ ተወዳዳሪዎች /short list firms/ ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ሥራ ላይ ለመወዳድር ፍላጎትና በቂ ልምድ ያላቸው ቅደመ መረጣ ለማድረግ የሚያስፈለጉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በማቅረብ ፍላጎታችሁን እንድትገልጹ ይጋብዛል፡፡
- በዘረፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡትን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- ከዚህ በፊት በዲዛይን ሥራና ማማከር ሥራ በቂ ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለማማክር ሥራ ሊያሰማራቸው የሚችሉ ቁልፍ ባለሙያዎች ያሉት እና የትምህረት ዝግጅትና የሥራ ልምዳቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- ሌሎች ለቅድመ መረጣ /ውድድር ላይ ያግዛሉ የሚባሉ የድርጅቱን የመፈፀም አቅም ደረጃና መስሪያ ቁሳቁስ የሚያስረዱ ማስረጃዎችን የሚያቀርቡ፡፡
- ሥራውን ለመስራት ፍላጎት ያላቸው አማካሪ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በየ ገጹ የድርጅቱን ማህተምና ሙሉ አድራሻ በመግለፅ ከማመልከቻ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያልተደረገበትና ማመልከቻ የሌለው የፍላጎት መግለጫ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የአካባቢ ማህበራዊ ተፅዕኖ ሰነድ በክልሉ መመሪያ ቁጥር 001/2010 መሰረት ፈቃድ ላለው አካል /sub contractor/ ሰጥቶ ማሰራትና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ሲሆን ይህ የፍላጎት መግለጫ /Expression of Interest/ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ09/03/2017 እስከ 24/03/2017 ባለው ተካታታይ ቀናቶች በወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና/ፋ/ ንብ/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 ተገኝተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም የቅድመ መረጣ ሥራ ፋላጎት የመጨረሻ ቀን 24/03/2017 4፡00 ቅድመ መረጣ ማድረግ ይጀምራል፡፡ ቅድመ መረጣው እንደተጠናቀቀ ላለፉትና ለተመረጡት /short list firms/ የመወዳደሪያ ሀሳብ መጠየቂያ ሰነድ ይሰጣቸዋል፡፡
- የፍላጎት መግለጫ ሰነዱ በድርጅቱ ህጋዊ ማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ፅሁፍ መኖር የለበትም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ተጨማሪ ማብራያ ካስፈለገ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓትበአካል በመገኘት ወይም በሥልክ ቁጥር 033 331 03 22 /033 331 18 61/ 033 333 13 31 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ