ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
10

በማከላዊ ጎንደር በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ከ01/11/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውል መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዓ/ህግ ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. መኪናው የሚፈልጋቸውን ወጭዎች ከናፍጣ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ባለንብረቱ (ባለሃብቱ) የሚሸፍን ነው፡፡
  5. ከሀምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30 /2019 ዓ/ም ድረስ ውል ሊወስድ የሚችል፡፡
  6. የመኪና ሊብሪ ያላቸው ሆኖ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ዋጋ በሞላ ተወዳዳሪ አሸናፊዉን የሚለይ ይሆናል፡፡
  7. የመኪናው የምርት ዘመን ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የሆነ እና መኪናው 45 ወንበር እና ከዚያ በላይ የሆነ፡፡
  8. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው ከወጣበት ከየካቲት 02/2018 ዓ/ም እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  10. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የካቲት 17/2018 3፡30 ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪላቸው ባሉበት የሳንጃ የመ/ደ/ሆስፒታል አዳራሽ በ- የካቲት 02/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባይኖርም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ ጠቅላላ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናልና ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. አሸናፊ ድርጀት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡
  16. ሆስፒታሉ የሚገኛዉ ሰርቢስ ከሚጀምርበት ቦታ ጀምሮ 3 ኪ/ሜ እርቀት አለዉ በመሆኑም ጠዋት 1፡50 ወደ ስራ ለምሳ 6፡30 ከምሳ መልስ 8፡20 እንዲሁም ማታ ወደ ቤት 11፡30 በድምሩ 4 /አራት/ ዙር እና እሁድና ቅዳሜ 2፡30 ወደ ቢሮ 11፡30 ወደ ቤት በድምሩ ሁለት ዙር ማመላለስ አለበት፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለዋስትና የሚያዘው ሲፒኦ በቁጥርና በፊደል የተጻፈው የተለያየ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 19 85 88 /09 39 24 50 07 /058 273 03 94 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here