ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዋድላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሆን በሰቆጣ ቃል ኪዳን ድርጅት የአምባ ጋሸና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የታድላ መንደር ቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የቁርቁር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ስራን ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ድርጅቶች ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለጨረታዉ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ግን በግን/አስ/ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራቾች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ውጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 ወይም 09 80 51 37 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here