የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 02/2018 እስክ የካቲት 16/2016 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 31 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ድምር ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገ/ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 16/2018 ዓ.ም 4፡30 ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውጤቱን በጠቅላላ ድምር ውጤት ያያል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደ/ከ/ስ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

