በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ላለዉ ዉሃ ጽ/ቤት ዉሃ ግንባታ አገልግሎት የሚዉል የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና የሙያ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥዉ መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይንት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከገንዘብ ያዥች ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ባንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ የካቲት 17/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 የካቲት 17/2018 ዓ.ም 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 270 05 97 /194 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

