ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

የግዥ መለያ ቁጥር 24/2018

ሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢትርፕራይዝ ለተማሪዎች አግልግሎት የሚውል  ጥሬ አተር እና ጥሬ ጎመን ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  2. በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢተርፕረይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት  የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢተርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈውን ጤፍ የወዝአደር ማውረጃን ጭምር ራሱ ችሎ ዩኒቨርስቲዉ ግቢ ድረስ በራሳቸዉ ወጭ  በማቅረብና ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ  ለጥሬ አተር ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ለጥሬ ጎመን ዘር ብቻ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉ ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጫራቾች ከመክፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የምንከፍት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 ቀን በኃላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ኢተርፕራይዙ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 11 59 13 56 ወይም 09 13 42 26 44 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here