ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በሰሜን ጎጃም አስተዳደር ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ የዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት አጠቃላይ ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ማለትም፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃ እንዲሁም ሎት 4. የኤሌክትሪክ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የሚችሉ ማንኛውም  ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ጨምሮ  ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ  የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል  ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ዝርዝር መረጃ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በየምድቡ (በየሎቱ) በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሽግ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ  የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢ/ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡  በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ በተላለፉት ዉሣኔዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናል፡፡ የመክፈቻዉ  ቀን  በዓል  ከሆነ በቀጣይ የስራ  ቀን የሚከፈት  ይሆናል፡፡
  1. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸበፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ በተባለዉ ቀን ዉስጥ ውል የማይዝ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡
  1. ጨረታዉ  የሚካሄደው  በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም የተጠየቀዉን ስፔስፊኬሽን በራሱ መቀየር አይቻልም ስርዝ ድልዝ የበዛበት መሆን  የለበትም፡፡ በስህተት ከተሠረዘ  በማያጠራጥር ሁኔታ  ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  2. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ  እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ  የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብና ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  3. የሠነድ መሸጫ ዋጋ ለእያንዳንዱ  ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል  ሠነድ መግዛት  ይችላሉ፡፡
  4. መ/ቤቱ ባወጣዉ ጨረታ ላይ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ሁሉም ተጫራቾች  የግዥ ደንብና መመሪያን   ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በአካል ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በስልክ 058 223 07 52  መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here