ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

በሰሜን ጎጃም ዞን የይልማ ዴንሳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለይልማ ዴንሳ ወረዳ እንስሳት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉል የሞሰቦ ቀበሌ የእንስሳት ክኒሊክና ቢሮ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛዉም ተጫራች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጽዳት ዕቃዎች ግዥው ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ የመንገድ ጥገናዉ ከደረጃ 7 እና ባላይ ያሉ ሆነዉ በመንገድ ስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 338 02 98 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሽህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ የሚኖርባቸው ሲሆን ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 8/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 29/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን፣ የንግድ ፈቃዳቸውንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ጨረታዉ የሚዘጋበት የካቲት 30/2018 ዓ.ም 3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ የካቲት 30/2018 ዓ.ም 4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ የለም፡፡
  11. አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች አሸገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  13. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  14. ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት /በጠቅላላ ዋጋ/ ነዉ፡፡
  15. ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  18. ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  19. የመንገድ ጥገና ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ነዉ፡፡
  20. ተጫራቾች ከደረጃ 9 እና በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡

የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here