ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 እስቴሸነሪ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒስ፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች ሎት 5 የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 6 ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 7 ደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 8 ናፍታ እና ቤንዚን ትራንስፖርት እና ሎት 9 የመኪና የሞተር ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ  ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. /የቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት  ቢሮ ቁጥር 07  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በአየር ላይ ከ9/03/2017 ዓ/ም እስከ 23/03/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ9/03/2017 እስከ 23/03/2017 ድረስ ማስገባት ይቻላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 24/03/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30  ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  13. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here