ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

የቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለቋሪት ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (ለሁለተኛ ጊዜ) እና ሎት 2 የህንጻ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ ተጫራቾች (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቋሪት ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3:00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት 3፡30 ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተባለው ሰዓት ይታሸግና ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ጽ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
  11. በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ፓራፍ ማድረግ አለበት፡፡
  12. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎች እና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል መያዝ አለበት፡፡
  14. የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ካቀረበው ድርጅት ሲሆን ከአንድ ሎት ከፋፍሎ መሙላት ወይም መጫረት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  15. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበው ዕቃ በፍተሻ የሚገባ መሆኑን ከወዲሁ ማወቅ አለበት፡፡
  16. አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ ቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  17. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 46 02 26 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቋሪት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here