ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
21

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡- የእህል ምርት ውጤቶች (አንደኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
  5. የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
  7. የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኙት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ከት/ቤቱ ገ/ያዥ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ መቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነበር፣ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው የካቲት 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን የካቲት 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ መኖር የለበትም፡፡ ነገር ግን ስርዝ ካለው ፓራፍ (ፊርማ) መኖር አለበት፡፡
  13. ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  14. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ምርቱን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
  15. ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኙ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
  17. አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here