የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1. የተለያዩ የውሃ ቆጣሪዎች፣ ሎት 2. የአፈር ቁፋሮ አገልግሎት ሰራ፣ ሎት 3. የቀን (የጉልበት) ሰራተኛ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል ኦርጅናሉን፣ ኮፒውን እና ሲፒኦ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (un Conditional Bank Garanty) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡
15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 20 50 79 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

