በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 እስቴሸነሪ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒስ፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች ሎት 5 የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 6 ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 7 ደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 8 ናፍታ እና ቤንዚን ትራንስፖርት እና ሎት 9 የመኪና የሞተር ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- /የቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ከ9/03/2017 ዓ/ም እስከ 23/03/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ9/03/2017 እስከ 23/03/2017 ድረስ ማስገባት ይቻላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 24/03/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት