በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኛው ሴ/መ/ቤቶች በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የበጀት ድጋፍ፣ ሎት 1 ጃ/ወ/ሚሊሻ ጽ/ቤት መ/ብርሃን ከተማ የሚሊሻ ካምፕ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት፣ ሎት 2 ጃ/ወ/ማህበራት ጽ/ቤት ዶሮና ቀበሌ የማህበራት መጋዝን ግንባታ በእጅ ዋጋ ማስገንባት እና ሎት 3 ጃ/ወ/ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት በመ/ብርሃን ከተማ ሰለሞን አዳራሽ ወንበር ተከላ እና ግዥ በሙሉ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፍል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የህንፃ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በህንፃ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የግንባታው አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ ነጥብ አምስት በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ማለትም ከ09/03/2017 ዓ/ም እስከ 29/03/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ09/03/2017 ዓ.ም ዓ.ም እስከ 29/03/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 30/03/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም ካለውም ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 /24 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት