ግልጽ የጨረታ ማስታወቃያ

0
53

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለነባሩ ጭልጋ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው አንከር አደዛ ጤና ጣቢያ የደረጃ ማሻሻል (ማሳደግ) ባለ ሶስት ብሎክ ተጀምሮ የቀረ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. በጥቃቅን ለተደራጁ ተጫራቾች እንደ ማንኛውም ተጫራች እኩል የሚጫረቱና ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው መሆኑንና መጫረት ለሚችሉ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ ሰውነት እና መተዳደሪያ ደንብ ከሰነዳችው ጋር ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እና አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በድጋፍ የሚያቀርብ ከሆነ ከተደራጅበት ጽ/ቤት ህጋዊ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን ህጋዊ ዶክመንትና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ግንባታው ከብር 200,000 (ሁሉት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተቋራጮች የሚጋበዙ ይሆናል፡፡
  7. የቅድሚያ ክፍያን በተመለከተ ለተቋራጮች በውሉ መሰረት ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ጋር እኩል ዋጋ ያለው የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ሲኖርባቸው ነው ወይም በራሳቸው ወጭ ሚሰሩ ከሆነ ወደ ሥራ ከገቡ በኃላ በሰሩት ሥራ ልክ በመሀንዲሱ እየተረጋገጠ ክፍያ የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. የሚያቀርቡት ንግድ ፈቃድና ቲን ግልጽ እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-9 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  11. ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በነ/ጭ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዝርዝር ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለተከታታይ 21 ቀናት በጋዜጣ ይውላል፡፡ በ22 ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከቀኑ 8፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ይህ ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን 8፡00 ታሽጓ 8፡00 ይከፈታል፡፡ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ውል ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ተጫራቾች ከአደራጃቸው ጽ/ቤት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. ጨረታውን ሲሞሉ ቫት ከእያንዳንዱ ዮኒት ፕራይስ ሳይሆን ከጥቅል ድምር ላይ ብቻ ማውጣት ይኖርባቸዋል፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 05 83 33 03 26 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  17. የድርጅትዎት ማህተም በየገፁ ማድረግውን አይዘንጉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የ2018 ዓ/ም የታደስ ንግድ ፈቃድ እና የደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለመሆናቸው የሚገልጽ ሰርተፊኬት ኮፒ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታ ሲሞላ ከእያንዳንዱ ዩኒት ራይስ ሳይሆን ከጠቅላላ ድምር ላይ  ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ጽ/ቤቱ ምንም አይነት ግብአት የማያቀርብ መሆኑ እናሳውቃለን፡፡

የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here