ግልጽ የጨረታ ማስታወቅያ

0
84

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2017 በጀት አመት ሎት 1 ኮፒውተር እና ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በ2017 ዓ.ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ለሚገዙት ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የአነ/ወ/ፍ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ድረስ እስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ 16 በ16ተኛው ቀን 3፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባይገኙም ሳጥኑን መክፈት የማንስተጓጎል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታ ሄደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  9. የጨረታ ሳጥን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ወይም /እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑን ታውቆ የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ሃያ በመቶ ሊጨምር /ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  13. አሸናፊው ድረጅት ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት በአነ/ወ/ፍ/ቤት አጎጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቹ በጨረታው ለመወዳደር ላወጣው ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  16. የመጫረቻ ሰነዱ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  17. አሸናፊ ድርጅቱ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  18. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም፡፡
  19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 63 74 68 17 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአነደድ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here