ግልጽ የጨረታ ማስታወቅያ

0
63

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት አመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃዎች እንዲሁም የብስክሌት ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የአገልግሎት መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፓስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዕለት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በጋዜጣ የሚውል ሲሆን በ16 ተኛው ቀን ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ እለት በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚህ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here