በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሊቦ ከምከም ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 2 የሞተር ዘይት፣ ሎት 3 የመኪና የእጅ ዋጋ ጥገና፣ ሎት 4 የኮንሰትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 5 ብሎኬትና ግማሽ ክብ ከአርማታ የተሰራ ዲች ከተጫራቾች መካከል በማወዳደር በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫሪቾች የጨረታ ሰነዱን ለእንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ሊቦ ከም/ወ/ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1 ብር 20,000 (/ሃያ ሽህ ብር)፣ ሎት 2 ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር) እና ሎት 3 ብር 10,000 (አሰር ሽህ ብር)፣ ሎት 4 ብር 30,000 (ሳላሳ ሸህ ብር)፣ ሎት 5 ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሸህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ እና ከሰነዱ ጋር ኮፒ መያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት እስከ 11፡30 ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሊቦከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተዘጋጀው ሳጥን እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ15ኛው ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ ግዥ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አካል የሚለየው በጥቅል ነው፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈውን እቃ ሊቦከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድርስ ማድረስ አለበት፡፡
- ጨረታው ሥርዝ ድልዝ ሰይኖርው እና እንዲነበብ ተድረጎ መሙላት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሁሉም ሎቶች በተጠየቁት ጥራት ስፔስፊኬሽን መሰረት በባለሙያ ተፈተሾ ማሰረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 01 95 /931 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

