የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ጨረታ ማስከበሪያ 00 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡፡ ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ታጫራቾች አገልግሎቱን ወይም ጥገናውን በደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ መስጠት የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት ፀንቶ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት / በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል