በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ የመካነ ኢየሱስ የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀትና ከዉስጥ ገቢ ከሚገኝ በጀት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ ምድብ 1. አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ምድብ 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ምድብ 3. ቋሚ መሳሪያ እቃዎች፣ ምድብ 4. የኤሌክትሪክ እና የዉሀ መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ምድብ 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ምድብ 6. የፈርኒቸር ዉጤቶች፣ ምድብ 7. የህትመት ሥራዎች እንዲሁም ምድብ 8. የህክምና ዕቃዎች መለዋወጫ እና የደንብ ልብስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጨኑ በእያንዳንዱ ምድብ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ካላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማስረጃቸዉን የዋናዉን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ አብረዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታዉ አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሰረት የነጠላ ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋዉን በመሙላትና በየገፁ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በፖስታ መታሽግ አለበት፡፡ ጨረታዉ ለ15 ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16 ተኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ዉስጥ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ሆስፒታሉ ጨረታዉን የመክፈት መብት አለዉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 70 00 39 00 ወይም 09 23 04 27 90 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የሥራ ዘርፍ ሁሉንም አይተሞች ወይም ዝርዝሮች መሙላት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ በጥቅል ድምር ዋጋ ይታያል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸዉን ዕቃዎች በስፔስፊኬሽናቸዉ መሰረት እና በሞለዉ ዋጋ መሰረት ከሆስፒታሉ ድረስ በራሱ ወጭ ማምጣት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ በተባለዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት እና በሞላዉ ዋጋ መሰረት ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ የግዥ መመሪያዉ በሚያዘዉ መሰረት ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን ለመጨመር ቢፈልግ የዋጋ ልዩነት እና የእቃ ልዩነት ሳይኖር ከየምድብ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋዉ 20 በመቶ መጨመር የሚችል ሲሆን የማይፈልጋቸዉ እቃዎች የበጀት ችግር ቢያጋጥመዉ ከየምድብ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋዉ 20 በመቶ መቀነስ ይችላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፋቸውን እቃዎች በስፌስፊኬሽናቸው መሰረት ከሆስፒታሉ እስቶር ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
መካነ-እየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

