ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
53

የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የጥበቃ ሥራ አውት ሶርስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈታድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
  7. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች አገልግሎቱን ወይም ጥገናውን በደ/ማ/ከተማ ላይ መስጠት የሚችሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱ ሥርስ ድልዝ መሆን ውድቅ ያደርጋል፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሃደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here