የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን የፈ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ለሚያሰራው ሎት 1 የዲች ቦይ 603 ሜትር እና ሎት 2. የዲች ቦይ 365 ሜትር ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መመሪያዎችን ያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ካርድ ወይም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የተቋራጮች የብቃት ሰርተፊኬት እንዲሁም አድራሻቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ለውጥ ማድረግ ወይም እራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለወደፊት ከመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረግ ሲሆን ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ የባንክ ሲፒኦ (የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 10፡00 ድረስ ሰነዱን ፈ/ከ/አስ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የውል ማስከበሪያ 25 በመቶ የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
- ተጫራቾች የግንባታውን ስፔስፊኬሽን እና ዲዛይኑን ከሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡
- ተጫራጮቾች በዘርፉ ልምድ የላቸውና ከሰሩበት መ/ቤት የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሶስትኛ ወገን በመሞላው የዋጋ ሙሌት ትንተርሰው መሙላት አይቻሉም፡፡ ሞልቶ ቢገኝም የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ አከፋፈት ቅሬታ ካላቸው ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ ቀናት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት /ተቋራጭ/ የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች (ተቋራጮች) ምንም አይነት የፍ/ቤት እገዳ ወይም የዲሲፒሊን ክስ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ወይም ኦርጅናል እና በኮፒ ማስረጃ በማድረግ ሁለት ፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተቋራጮች ጠቅላላ ስራ ተቋራጭና የመንገድ ሥራ ተቋራጭ መሆን አለባቸው፡፡
- ስለ ጨረታው የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ 09 12 50 91 06 ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይችላሉ፡፡
የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

