ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
128

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረታቦር አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽዳት እቃዎችን ፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃ ፣ የኤሌክተሮኒክስ ጥገና ፤ የዉሃ ቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን የተለያዩ ህትመቶችን ፤ የሙያተኞች የፕላስቲክ ዶክተር ሹዝ ጫማና የፕላስቲክ ቦት ጫማዎችን፣ ሁለገብ ጥገና እቃዎች፣ የተለያዩ ብትን ጨርቆች፤ ለሙያተኞችና ለበሽተኞች አገልግሎት የሚውሉ የመብራት መለዋወጫ እቃዎች የተለያዩ ፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ /የሥራ/ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉን በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍና ማህተም ፣ ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከግ/ፋ/ን/አስ//ቡድን ቢሮ ዉስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ-1 በመክፈል ማስያዝና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲ.ፒ.ኦ ከሆነ ዋናዉ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በአንድ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በደ/ታቦር ሆስፒታል ውስጥ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታዎቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ፖስታውን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በ16ኛው ቀን የበዓል እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ ባለዉ አምስት /5/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ዉል መዉሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
12. አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
13. አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዕቃ በራሳቸው ወጭ ሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸው፡፡
14. ተጫራቾች ለውድድር ከቀረቡ በኋላ ሀሣባቸውን መለወጥ/ማሻሻል/ ወይም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
15. ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት/ በስ.ቁጥር 058 441 16 57 ፣09 20 44 22 25 ፣ 09 18 19 51 75 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
16. ተጫራቾች ሆ/ሉ አስፈላጊ ሆኖ ካገኝ አሸናፊውን በጥቅል ድምር ሆነ በተናጥል የመለየት አለው ነገር ግን በጥቅል ለመለየት የማይገደድ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የደብረታቦር ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here