በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ የመካነ ኢየሱስ የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 የበጀት ዓመት በመደበኛ በጀትና ከዉስጥ ገቢ ከሚገኝ በጀት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎችን በምድብ ወይም በሎት የተከፈሉትን እቃዎች ሎት 1 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 ኤሌክትሪክና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ሎት 5 የህትመት ሥራ ውጤቶች፣ ሎት 6 የፈርኒቸር ውጤቶች፣ ሎት 6 ቋሚ መሳይ እቃዎች እና ሎት 7 የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈልቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጨኑ በእያንዳንዱ ምድብ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማስረጃቸዉን የዋናዉን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ስለጨረታዉ አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 28 በማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ወይም ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ በማስያዝ በደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ አብረዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሰረት የነጠላ ዋጋ እና የጠቅላላ ዋጋዉን በመሙላትና በየገፁ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 በመገኘት ፖስታዉን ማስገባት ይቻላል፡፡ ጨረታዉ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ዉሎ በዚሁ ቀን በ11፡40 ታሽጎ በነጋታዉ በ16 ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ዉስጥ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ሆስፒታሉ ጨረታዉን የመክፈት መብት አለዉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 17 30 15 ወይም 09 23 04 27 90 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የሥራ ዘርፍ ሁሉንም አይተሞች ወይም ዝርዝሮች መሙላት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በጥቅል ድምር ዋጋ ይታያል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት ያሸነፋቸዉን ዕቃዎች በስፔስፊኬሽናቸዉ መሰረት እና በሞለዉ ዋጋ መሰረት ከሆስፒታሉ ድረስ በራሱ ወጭ ማምጣት የሚችል፡፡ በተባለዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት እና በሞላዉ ዋጋ መሰረት ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ የግዥ መመሪያዉ በሚያዘዉ መሰረት ተጠያቂ መሆን አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን ለመጨመር ቢፈልግ የዋጋ ልዩነት እና የእቃ ልዩነት ሳይኖር ከየምድብ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋዉ ሃያ በመቶ መጨመር የሚችል ሲሆን የማይፈልጋቸዉ እቃዎች /የበጀት ችግር ቢያጋጥመዉ/ ከየምድብ ከጠቅላላ የግዥ ዋጋዉ ሃያ በመቶ መቀነስ ይችላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ ጨረታዉን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀን በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ የግዥን የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ በፍትህ ዉል መያዝ ይኖርበታል፡፡
የመካነ ኢየሱስ የመጀሪያ ደረጃ ሆስፒታል