የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ በመክፈል ወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 21 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳዳሩበት የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱንና ንግድ ፈቃዱ በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጨረታው በወጣው ማስታወቂያ መሠረት 20 በመቶ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን ወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ውድድሩ በጥቅል ነው፡፡
- ጨረታው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 446 13 45 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የሚሞሉት ነጠላ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
የወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት