የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉል የተለያዩ ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የሚሳተፉ ተጫራቾች (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው 15 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ቡድን ቢሮ ጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ቡድን በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

