የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት 1 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 ፈርኒቸር፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5 ጽዳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዛው እቃ ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከህዳር 3/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ፖስታው በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በታሸገ ፖስታ ባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ካሸነፉበት ቀን ጀምረው ውል በመውሰድ ሥራ መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች እኛ በሠጠናቸው ዋጋ አሸንፈው በሚመለከተው መሠረት የእያንዳንዱን እቃ (አገልግሎት) ብዛት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ዝቅተኛ ጠቅላላ ዋጋ ድምር ያቀረበዉን ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 21 ወይም ስልክ ቁጥር 058 226 65 11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

